Daily Weather Report 24 Nov 27

Weather Summary for previous day

Nov. 26, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በጎንደር፣ ቻግኒ፣ ደብረማርቆስ፣ በጊዳ አያና፣ በአይራ፣ በበደሌ፣ ማሻ፣ በጅንካ፣ ምዕራብ አባያ፣ ኮንሶ እና ጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎሬ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in west Amara, Benshangul Gumuz, west Oromia, Southwest and South Ethiopia areas of our country. In this regard, Debarak, Gondar, Chagni, Debremarkos, Gida Ayana, Aira, Bedele, Masha, Jinka, Mirab Abaya, Konso and Jinka received light to moderate (1-29 mm) rain. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Gore.

Weather Forecast for next day

Nov. 28, 2024

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፣ በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ በመነሳት የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጎባ፣ በኮንታ ኮይሻ፣ በባስኬቶ፣ በመልኮዛ እና በአሪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southwest, south and southeast areas of our country and due to the occasional intensifying weather events the northeastern parts of the country will have cloud cover. In association with this, from Oromia region Guji and west Guji, west Arsi, Bale and east Bale, Borena and east Borena zones, as well as Jimma and Ilubabor zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Fafa, Konta, West Omo and Dauro zones; from Gambella region Agnouak and Majang zones; zones of Sidama region; from southern Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Derashe, Amaro, Burji, South Omo and Gedeo and from Somali region Liben, Afder, Korahe and Shebelle zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Goba, Konta Koisha, Basketo, Melkoza and Ari, will receive reciev heavy amounts of rain of more than 30 mm in 24 hours.