Daily Weather Report 24 Nov 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደባርቅ፣ አዴት፣ ቻግኒ፣ ደብረማርቆስ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ሊሙገነት፣ ቦሬ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ጋምቤላ፣ ማሻ፣ አማን፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ጂንካ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, Debark, Adet, Chagni, Debremarkos, Gimbi, Nekemte, Arjo, Limugenet, Bore, Gore, Bure, Gambella, Masha, Aman, Wolayta Sodo, Arba Minch, and Jinka had cloud cover. In this regard, light to moderate (1-29 mm) amounts of rain were recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዶሎ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ኤረር እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጎደሬ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በጎባ እና በሳላማጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the south and southeastern areas of our country and the western and southwestern areas of the country, which are their second rainy season of Bega. In association with this, From Oromia region Guji and west Guji, west Arsi, Bale and east Bale, Borena and east Borena zones, as well as Jimma and Ilubabor zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones of the; from Gambella region Anuak and Majang zones; zones of Sidama region; from the southern Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Derashe, Amaro, Burji, South Omo and Gedeo zones and from Somali region Doolo, Korahe, Shebelle, Erer and Liben will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Godere, Masha, Yeki, Goba and Salamago will receive heavy amounts of rain of more than 30 mm in 24 hours.