Daily Weather Report 24 Nov 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በማዕከላዊ ትግራይ፣ በምዕራብ አማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን የነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአድዋ፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በደባርቅ፣ በጎንደር፣ በአይከል፣ በሻሁራ፣ በዳንግላ፣ በአየሁ፣ በላይበር፣ በፓዊ፣ በአሶሳ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በነቀምቴ፣ በአለምተፈሪ፣ በሞያሌ፣ በጋምቤላ፣ በማሻ እና በጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በባህር ዳር፣ በቻግኒ እና በጊዳ አያና በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the central Tigray, west Amhara, Benishangul-Gumuz, west and south Oromia, Gambella, Southwest and South Ethiopia. In this regard, Adwa, Shirendesilase, Debark, Gondar, Aykel, Shahura, Dangla, Ayehu, Leiber, Pawi, Assosa, Nejo, Gimbi, Nekemte, Alemteferi, Moyale, Gambella, Masha and Jinka received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy amounts of more than 30 mm in 24 hours were recorded in Bahir Dar, Chagni and Gida Ayana.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የአፍዴር እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጎደሬ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በጉራፈርዳ፣ በመልኮዛ እና በሳላማጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በአቸፈር፣ በቁምቢ እና በፊቅ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አከባቢዎች ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን መሠብሠብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል።
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern areas of our country which are their second rainy season of Bega, as well as western and southwestern parts of the country. In association with this, from Oromia region Guji and west Guji, east Bale, Borena and east Borena; Jima, Ilubabor, Buno Dele, Kelem and East Wolga zones; from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from the Southern Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Derashe, Amaro, Burji, South Omo and Gedio zones and from Somali region Afder and Liben zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Godere, Masha, Yeki, Guraferda, Melkoza and Salamago will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, Dangla, Chagni, Achefer, Kumbi and Fiq will receive light amounts of unseasonable rainfall. The Ethiopian meteorology institute suggests that there is a need for communities to collect harvest crops in areas where there is unseasonal rain.