Daily Weather Report 24 Nov 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ማንኩሽ፣ ፓዌ፣ ቡለን፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ አደሌ፣ ጃራ፣ ቡሌሆራ፣ ያቤሎ፣ ቦሬ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, Debark, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Dangila, Mankush, Pawe, Bullen, Gore, Jimma, Bedele, Aira, Gimbi, Nekemte, Shambu, Adele, Jara, Bulehora, Yabelo, Bore, Hawassa, Dilla, Walaita, Sodo, Arba Minch, Sawula, Jinka, Konso and Burji had cloud coverage and received light to moderate rain.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላ ዙሪያ፣ በሳለኖኖ፣ በሰዮ፣ በቡሬ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በገሻ፣ በጎደሬ፣ በመኒት ሻሻ እና በሐመር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሁመራ፣ በወልቃይት፣ በዳንሻ፣ በፀገደ፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በፀለምት፣ በደባርቅ፣ በመተማ፣ በአርማጮ፣ በደምቢያ፣ በጎንደር፣ አይከል፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በአለፋ፣ በጣቁሳ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በአቸፈር፣ በሞጣ እና በሜጫ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, favorable weather conditions for rains will persist the same way over the south and southeast areas of our country, which are their second rainy season of Bega and in the western and southwestern parts of the country. In line with this, a few Guji and Borena zones of Oromia region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east Wellega zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Asosa and Kamash zones; from south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from south Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, Konso, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Itang and Majang zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall will be experienced in Gambella Zuria, Salenono, Sayo, Bure, Masha, Yeki, Gesha, Godere, Menit Shasha and Hamer within 24 hours. On the other hand, due to the strengthening weather events, Humera, Welkait, Dansha, Tsegede, Shire Endesilase, Tselemt, debark, Metema, Armacho, Dembiya, Gondar, Ayikel, Fogera, Bahirdar, Alefa, Takusa, Jawi, Dangila, Chagni, Achefer, Motta and Mecha will receive light unseasonal rainfall.