Daily Weather Report 24 Nov 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባህር ዳር፣ በማንኩሽ፣ በቡለን፣ በሻምቡ፣ በአንገርጉትን፣ በጊምቢ፣ በአይራ፣ በደምቢ ዶሎ፣ በጎሬ፣ በጋቲራ፣ በጭራ፣ በአደሌ፣ በጃራ፣ በቦሬ፣ በጋምቤላ፣ በፉኝዶ፣ በማሻ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሳውላ፣ በጅንካ፣ በምዕራብ አባያ፣ በብላቴ እና በዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the west Amhara, Benishangul-Gumuz, west and south Oromia, Gambella, Southwest Ethiopia and Southern Ethiopia. In this regard, they received light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall in Bahir Dar, Mankush, Bullen, Shambu, Angergut, Gimbi, Aira, Dembi Dolo, Gore, Gatira, Chira, Adele, Jara, Bore, Gambella, Fugnido, Masha, Arba Minch, Sawla, Jinka, Mirab Abaya, Bilatte and Dilla.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መኖር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች እና የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለም እና ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጎደሬ፣ በሸኮ፣ በጉራፈርዳ፣ በደቡብ ቤንች፣ በሱራማ፣ በማጂ፣ በሳላማጎ፣ በደቡብ አሪ እና በዲሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዳንግላ፣ በጓንጓ፣ በፋግታለኮማ፣ በወንበርማ፣ በቡሬ፣ በሰከላ፣ በጃቢጠናን፣ በደቡብ ሜጫ፣ በይልማናደንሳ፣ በባህር ዳር ዙሪያ፣ በደምበጫ፣ በሁለቱጅነሴ፣ በማቻከል፣ በሰናን፣ በጉዛመን፣ በሊቦከምከም፣ በፎገራ፣ በደራ፣ በአንዳቤት፣ በምስራቅ እስቴ፣ በፋርጣ፣ በእብናት፣ በአለፋ፣ በጣቁሳ፣ በመተማ፣ በደምቢያ፣ በጎንደር ዙሪ፣ በአርማችሆ፣ በዳባት፣ በደባርቅ፣ በጠገዴ፣ በቆቦ፣ በጊዳን፣ በጉባላፍቶ፣ በወረባቦ፣ በኩታበር፣ በኩነባ፣ በበረሀሌ፣ በጸገዴ፣ በጸለምት፣ በአስገዴ፣ በዛና፣ በአዲዳሮ፣ በኢሮብ፣ በአጽቢ፣ በሸርካ፣ በሮቤ፣ በሴሩ፣ በጠና፣ በጮሌ፣ በመርቲ፣ በኖኖ፣ በጂባጥ፣ በኮቢ እና በግንደበረት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Weather events favourable for the presence of rain tomorrow will have better intensity over the south and southeast which are their second rainy season of Bega, as well as in the west and southwest areas of our country. In association with this, the Oromia region Borena and east Borena zones, Guji and west Guji zones, west Arsi, Bale and east Bale zones and the zones of Ilubabor, Jimma, Bunobedele, west, east, Kelem and Horogudru Wellga zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel and Kamash zones; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawro, west Omo, Konta and Kefa zones; from South Ethiopia region Gamo, Gofa, Wolaita, Derashe, Amaro, Burji, Baskete, Konso and Gedio zones from the Gambella region Majang and Agnuak zones and from Somali region Dawa, Liben, Afder and Shebelle zones will receive light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall. In addition, in Godere, Sheko, Guraforda, South Bench, Surama, Maji, Salamago, South Ari and Disa will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, in Dangla, Guangua, Fagtalekoma, Wemberma, Bure, Sekela, Jabitena, South Mecha, Yilmanadensa, Bahir Dar, Dembecha, Huletujnesse, Machakel, Senan, Guzamen, Libokemkem, Fogera, Dera, Andabet, Misrak Esite, Farta, Ebna, Alfa, Takusa, Metema, Dembia, Gondar Zuri, Armachiho, Dabat, Debark, Tegede, Kobo, Gidan, Gubalafto, Werebabo, Kutaber, Kunneba, Berhale, Tsegede, Tselemt, Asgede, Zana, Adidaro, Erob, Atsibi, Sherka, Robe, Seru, Tena, Chole, Merti, Nono, Jibat, Cobi and Gindeberet will receive light to moderate amounts of unseasonable rainfall.