Daily Weather Report 24 Nov 20

Weather Summary for previous day

Nov. 19, 2024

በትናንትናው ዕለት በጥቂት የምዕራብና ምስራቅ አማራ፣ምዕራብ፣ምስራቅና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ላይበር፣ ስሪንቃ፣ ጨፋ፣ ኤሊዳር፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ አርሲ፣ አደሌ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ፉኝዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ ምዕራብ አባያ፣ ኮንሶ እና ሳዉላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ ሲሆን በጋምቤላ እና አማን ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover in a few parts of West and East Amhara, West, East and South Oromia, Gambella, South West Ethiopia and South Ethiopia. In connection with this, Leiber, Srinka, Cheffa, Elidar, Nekemte, Arjo, Bedele, Gatira, Limugenet, Arsi, Adele, Bale robe, Bore, Bulehora, Negele, Yabelo, Moyale, Funedo, Arba Minch, Jinka, Mirab Abaya, Konso and Sawula. It receives light to moderate rainfall (1-29 mm). Heavy rains were recorded in Gambella and Aman.

Weather Forecast for next day

Nov. 21, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ የኢሉባቦር እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ጋሞ፣ጎፋ፣ ወላይታ፣ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዶሎ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of rains will have better strength over the North East, South West, West and East regions of the country. Along with this, from Oromia region Borena and East Borena zones, Guji and West Guji zones; Ilubabor and Jimma zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo, Konta and Kefa zones from South West Ethiopia region; Amaro, Gamo, Gofa, Wolayta, Derashe, Konso and Gedo zones of Southern Ethiopia region, Majang and Anuwak zones of Gambella region and Dolo zone of Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm).