Daily Weather Report 24 Nov 19

Weather Summary for previous day

Nov. 18, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደብረብርሀን፣ በሾላገበያ፣ በቡኢ፣ በደባርቅ እና በወረኢሉ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday they had the dry, sunny and windy weather of the summer over the northeastern, eastern and central areas of Our Country. At the same time, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Debre Berhan, Shola Market, Bui, Debark and Wereilu.

Weather Forecast for next day

Nov. 20, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የኢሉባቦር እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ጋሞ፣ጎፋ፣ ወላይታ፣ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ እና ቆራሄ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ስናን፣ ፍኖተ ሰላም፣ ሰከላ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ግምጃ ቤት፣ ጊቤ፣ ሆሳዕና፣ ሌሞ፣ አንገቻ እና ከምባታ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Tomorrow there will be strong cloud cover over the south and southeastern areas of our country and the southwest and east areas of the country, which are their second rainy season of Bega. At the same time, the Oromia region includes West Arsi, Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones, as well as Ilubabor and Jimma zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo, Konta and Keffa zones from the Southwest Ethiopia region; Amaro, Gamo, Gofa, Wolaita, Derashe, Konso and Gedeo zones; Majang Zone of Gambella Region; Zones of Sidama Region And from the Somali region, the zones of Liben, Dawa, Afder, Shebelle and Korahe will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall at many of their locations. In addition, based on the intensifying weather events, Senan, Finote Selam, Sekela, Debre Markos, Treasury, Gibe, Hosanna, Lemo, Angcha and Kembata will receive light to moderate amounts of unseasonable rainfall. On the other hand, the northeastern, central and eastern areas of our country will experience dry, sunny and windy weather in the Bega.