Daily Weather Report 24 Nov 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ጋምቤላ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጋምቤላ ከቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደብረብርሀን፣ በመሀል ሜዳ፣ በሾላገበያ፣ በቡኢ፣በጂጂጋ፣ በእንዋሪ፣ በአምባ ማርያም፣ በቡኢ፣ በቢሾፍቱ እና በአርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the Gambella. In this regard, light amounts of rainfall were recorded in Gambella. On the other hand, the northeast, east and central parts of the country were dominated by Bega season dry, sunny and windy weather conditions. In association with this, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Debre Birhan, Mehalmeda, Sholagebeya, Enwari, Amba Maryam, Jijiga, Bui, Bishoftu and Arsi Robe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ዞኖች እንዲሁም የኢሉባቦር ፣ጂማ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ጋሞ፣ጎፋ፣ዋለይታ፣ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ የቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በቦሰት፣በፋንታሌ፣ምነጀር ሾነከራ፣ጢዮ፣ዱግደ፣ቆቦ እና በዳሮለቡ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜንምስራቅ እና መካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸው ሲሆን በምስራቅ አማራ፣ በመካከለኛው ኦሮሚያ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud covers over the south and southeastern parts of our country which are the second rain season of Bega, and also the southwest and east regions of the country in line with this, from Oromia region west Arsi and Arsi, Bale and east Bale zones, Borena and east Borena, Guji and west Guji, as well as the Ilubabor ,Jimma and Bunno Badalee zones; from southwest Ethiopia region; Sheka,Benchi Shekko,west Omo and Kaffa, south Ethiopia Amaro, Gamo, Gofa, Walaita, Darashe, Konso and Gedi’o, and Fafa zones from Gambella region Anuak and Majang zones; and from Somali region Jarrar, Afder, Shebelle, Korah and Dolo zones, zones of Sidama region will receive of light to moderate (1-29) amount of rainfall in some places. In addition, based on the intensifying weather events, in Boseta, Fantale, Minjar Shenkora, Tiyo, Dugda and Darolebu will receive light to moderate amounts of unseasonal rainfall. On the other hand, the northeast and central parts of our country will experience dry and sunny and windy weather conditions, while forecast data suggest that the minimum temperature of the day will be below 5oC in the highlands of eastern Amhara and central Oromia.