Daily Weather Report 24 Nov 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎሬ፣ በጋምቤላ እና በማሻ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደብረብርሀን፣ በወገልጤና፣ በእንዋሪ፣ በቡኢ እና በአርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in western Oromia, Gambella and southwestern Ethiopia. In line with this, light amounts of rain were recorded in Gore, Gambella and Masha. On the other hand, the northeast and central parts of the country were dominated Bega season dry, sunny and windy weather conditions. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Debre Berhan, Wegeltena, Enwari, Bui and Arsi Robe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በበደቡብ ሶማሌ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢሉባቦርና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ማኦ ኮሞ ዞን፤ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ቆራሄና ሸበሌ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜን፣ ምስራቅ እና መካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው የሚውል ሲሆን በምስራቅ አማራ፣ በመካከለኛውና ደቡብ ኦሮሚያ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳይሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud cover in southern Somali, western Oromia, Benishangul-Gumuz, southwestern Ethiopia and Gambella. In association with this, Ilubabor and Kelem Wellega zones, Sheka and Bench Sheko zones, Mao Komo zone, Agnuwak and Majang zones and Korahe and Shebelle zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rain at a few places. On the other hand, the northern, eastern, and central parts of our country will be dominated by the Bega dry, sunny and windy weather conditions, and forecasts showing that the daily minimum temperature will be below 5oC in eastern Amhara, central and southern Oromia highlands and in the eastern highlands of the country.