Daily Weather Report 24 Nov 15

Weather Summary for previous day

Nov. 14, 2024

በትናንትናው ዕለት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በነጆ፣ አይራ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጋምቤላ እና ጅንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was cloud cover in Benshangul Gumuz region, West Oromia, Gambella and South Ethiopia. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Nedjo, Aira, Dele, Gore, Gambella and Jinka.

Weather Forecast for next day

Nov. 16, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ጋምቤላ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ የሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, West Oromia, Benshangul Gumuz, Southwest Ethiopia and Gambella will have cloud cover and accumulation. Along with this, Ilubabor, West and Kelem Wollega zones; Sheka and Bench Shako Zones; Asosa and Mao Como zones; Itang, Anuwak and Majang zones receive light to moderate rainfall (1-29 mm).