Daily Weather Report 24 Nov 14

Weather Summary for previous day

Nov. 13, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብና መካከለኛ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሞጣ፣ ቻግኒ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ ጭራ ፣ ሞያሌ፣ ጋምቤላ፣ ቡሬ፣ ጅንካ፣ ማሻ እና ጎዴ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday in West and Central Amhara; Benshangul Gumuz region, West and South Oromia, Gambella, South Ethiopia, South West Ethiopia, and Somalia had cloud cover. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Mota, Chagni, Asosa, Nedjo, Aira, Arjo, Nekemte, Chira, Moyale, Gambella, Bure, Jinka, Masha and Gode.

Weather Forecast for next day

Nov. 15, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የአፍዴር እና ዳዋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በተጨማሪም በማሻ፣ ማጃንግ ፣ መንገሽ እና ጎደሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, favorable weather events for the formation of rain will continue in the same way in the south and southeast areas of our country, which are the second rainy season of Bega, and in the west and southwest areas of the country. Along with this, from Oromia region Borena and East Borena, Guji and West Guji zones and Jimma, Ilubabor, West and Kelem Welega zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Asosa, Metekel and Maokomo zones from Benshangul Gumuz region; Gamo, Gofa, Amaro, Derashe, Konso and Gedo zones from Southern Ethiopia region; Itang, Anuwak and Majang zones from the Gambella region; Zones of Sidama Region and Afder and Dawa Zones of Somali Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. In addition, Masha, Majang, Mengesh, and Godere will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.