Daily Weather Report 24 Nov 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብና መካከለኛ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባህር ዳር፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አሶሳ፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ አርጆ፣ ጎሬ እና ሞያሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በ ማሻ በ24 ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday in West and Central Amhara; Benshangul Gumuz Region, West and South Oromia and Southwest Ethiopia had cloud cover. In relation to this, Bahir Dar, Dangla, Chagni, Asosa, Bullen, Pawe, Metekel, Gambela, Funedo, Gimbi, Nedjo, Arjo, Gore and Moyale received light to moderate (1-29 mm) rain and in Masha on 24 Heavy rainfall of more than 30 mm was recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አዊ፣ ግምጃ ቤት፣ አዴት፣ ባህር ዳር ዙሪያ፣ ደምበጫ እና ሰከላ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover in the south and southeast areas of our country, as well as in the west and southwest areas of the country, which are their second rainy season. Along with this, from the Oromia region West Arsi, Bale, East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones and Jimma, Ilubabor, West and Kelem Welega zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Asosa, Metekel and Maokomo zones from Benshangul Gumuz region; Zones of Sidama region and Liban, Dawa zones of Somali region receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in most of their areas. On the other hand, based on the intensifying weather events, Dangla, Chagni, Awi, Ghamja Bet, Adet, Bahir Dar Zuria, Dembecha and Sekela will receive light amounts of unseasonal rain.