Daily Weather Report 24 Nov 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብና መካከለኛ አማራ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ፤ ሲዳማ እና በሶማሌ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሻሁራ፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ላይበር፣ መተከል፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ሊሙ ገነት፣ አደሌ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ማሻ፣ አማን፣ አርባ ምንጭ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ ሽላቦ እና ዶሎኦዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday in West and Central Amhara; Benshangul Gumuz; West and South Oromia; Southwest Ethiopia; South Ethiopia; Sidama and Somalia they had cloud cover in. In connection with this, Shahura, Adet, Mota, Laiber, Metekel, Asosa, Gambella, Nekemte, Arjo, Limu Gent, Adele, Bulehora, Negele, Masha, Aman, Arba Minch, Sawula, Jinka, Konso, Dila, Bore, Shlabo and Doloodo. Light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚቀጥሉ ሲሆን እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ባሌ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የአፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ እና ዶሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰዮ፣ ጊዳሜ፣ አንፊሎ፣ ማጃንግ ፣ መንገሽ፣ ጎደሬ እና ማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, favorable weather conditions for the formation of rain will continue in the south and southeast areas of our country, which are the second rainy season of the Bega, and will have better strength in the west and southwest areas of the country. In connection with this, from the Oromia region of West Arsi, East Bale zones and Jimma, Ilubabor, West and Kelem Welega zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Asosa, Metekel and Maokomo zones from Benshangul Gumuz region; South Omo, Basketo, Amaro and Gedo zones from Southern Ethiopia region; Itang, Anuwak and Majang zones from the Gambella region; Zones of Sidama region and Afder, Shebele, Korahe, Nogob and Dolo zones of Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. In addition, Sayo, Gidame, Anfilo, Majang, Mengesh, Godere and Masha will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours.