Daily Weather Report 24 Nov 10

Weather Summary for previous day

Nov. 9, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሲዳማ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አይከል፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መተከል፣ አንገርጉትን፣ ቴፒ፣ ነቀምቴ፣ ሳውላ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ አርሲ እና ሞያሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡Yesterday there was cloud cover in West Amara, Benshangul Gumuz, South Ethiopia, Sidama, West and South Oromia parts of the country. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rains were recorded in Aykel, Dangla, Chagni, Metkel, Angergutn, Tepi, Nekemte, Sawula, Dila, Bore, Arsi and Moyale.

Weather Forecast for next day

Nov. 11, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover and accumulation in the south and southeast as well as west and southwest parts of the country, which will be their second rainy season. In connection with this, from the Oromia region of West Arsi, Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones and Ilubabor, West and Kelem Welega zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Asosa and Maokomo zones from Benshangul Gumuz region; Gamo, Gofa, South Omo, Basketo, Amaro, Derashe, Konso and Gedo zones from Southern Ethiopia region; The Itang, Anuwak and Majang zones of the Gambella region and the Sidama region zones receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in most of their areas.