Daily Weather Report 24 Nov 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኦሮሚያ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ጅማ፣ አደሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ቡሌሆራ እና ነገሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was cloud cover in Benshangul Gumuz, Gambella, South Ethiopia and South Oromia parts of the country. In relation to this, Asosa, Gambella, Abobo, Funedo, Jimma, Adele, Arba Minch, Bulehora and Negele recorded light to moderate (1-29 mm) rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚቀጥሉ ሲሆን እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በግምጃ ቤት ፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳም፣ ቻግኒ፣ ፍኖተ ሰላም ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, favorable weather conditions for the formation of rain will continue in the south and southeast areas of our country, which are the second rainy season of the Bega, and will have better strength in the west and southwest areas of the country. Along with this, from the Oromia region West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones and Jimma, Ilubabor, West and Kelem Welega zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Asosa, Metekel and Maokomo zones from Benshangul Gumuz region; Amaro, Derashe, Konso and Gedo zones from Southern Ethiopia region; Itang, Anuwak and Majang zones from the Gambella region; Sidama region zones and Liban, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer zones from Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. On the other hand, based on the intensifying weather events, you will get light amount of unseasonal rain in Gimja Bet, Enjbara, Addis Qadam, Chagni, Finote Salam.