Daily Weather Report 24 Nov 08

Weather Summary for previous day

Nov. 7, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በባህር ዳር፣ በቻግኒ፣ በጊዳያና፣ በአደሌ፣ በባሌሮቤ፣ በቦሬ፣ በጋምቤላ፣ በፉኝዶ፣ በማሻ፣ በሳውላ፣ በአርባምንጭ፣ በምዕራብ አባያ እና በዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the western Amhara, western and southern Oromia, Gambella, southwest and southern Ethiopia. In this regard, Bahir Dar, Chagni, Gidayana, Adele, Bale Robe, Bore, Gambella, Fugndo, Masha, Sawla, Arba Minch, Mirab Abaya and Dilla received light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall.

Weather Forecast for next day

Nov. 9, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰዮ፣ በሳለኖኖ፣ በማሻ እና በጋሸሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በግምጃ ቤት ፣ እንጅባራ፣ ዳሮ ለቡ፣ ቦኬ፣ በሀዊጉዲና፣ በቡርቃድህንቱ፣ በጠምባሮ፣ በሮቤ፣ በቁምቢ፣ በግራዋ፣ በመዩሙልቄ፣ በፈዲስ፣ በባቢሌ እና በሐረር ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be better cloud cover over the south and southeastern areas of our country which are the second rain season of Bega, as well as west, southwest and eastern parts of the country. In association with this, from Oromia region west Arsi, Bale and east Bale, Borena and east Borena, Guji west Guji zones and Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west, east and Kelem Wellega zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, west Omo and Kefa zones; from Benishangul-Gumuz region Assossa, Metekel and Maokomo zones; from southern Ethiopia region: Amaro, Derashe, Konso and Gedeo zones; from Gambella region Itang, Agnuak and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Liben, Dawa, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Jarrar, Dolo and Erer will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall at many places. In addition, in Seyo, Saleno, Masha, and Gashemo will receive heavy amounts of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, in Gimja Bet, Enjibara, Daro Libu, Boke, Hawigudina, Burqadhintu, Tembaro, Robe, Khumbi, Grawa, Meumulke, Fedis, Babile and Harar will receive light amounts of unseasona rainfall.