Daily Weather Report 24 Nov 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ፣ በምስራቅ አማራ፣ በአፋር እና በምስራቅ እና ደቡብ ኦሮሚያ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አጽቢ፣ ማይጨው፣ ላሊበላ፣ ወገልጤና ፣ ስሪንቃ፣ ጋምቤላ፣ ወራቤ፣ ጊኒር እና ሐረር ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in South and East Tigray, East Amara, Afar and East and South Oromia parts of the country. In relation to this, light to moderate (1-29 mm) rains were recorded in Atsbi, Maychiu, Lalibala, Wegeltena, Srinka, Gambella, Warabe, Ginir and Harer
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ፣ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል እናማኦኮሞ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ዶሎ እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, favorable weather events for the formation of rain will have a better strength in the south and southeast areas of our country, as well as in the west and southwest areas of the country, which are the second rainy season of Bega. In connection with this, from the Oromia region, West Arsi, Bale, East Bale, East Borena, Guji and West Guji zones, as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele and Kelem Welega zones; From South West Ethiopia region of Sheka, Bench Sheko, West Omo and Fefan, zones; From Benshangul Gumuz region of Asosa, Metekel and Mao komo zone; Amaro, Derashe, Konso and Gedo zones from Southern Ethiopia region; Itang, Anuwak and Majang zones from Gambella region; Sidama region zones and Liban, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Nogob, Dolo and Erer zones from Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places.