Daily Weather Report 24 Nov 06

Weather Summary for previous day

Nov. 5, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ቻግኒ፣ላይበር፣ አይራ፣ አርጆ፣ ኢጃጂ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ አደሌ፣ ቦሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ተርጫ እና ሳውላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ ደግም 33 ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover in the west, south west and south parts of the country. In this regard, Chagni, Leiber, Aira, Arjo, Ijaji, Bedele, Gore, Kara, Adele, Bore, Gambella, Funedo, Tepi, Aman, Tercha and Saula received light to moderate (1-29 mm) rainfall. ; A heavy rainfall of 33 mm was also recorded in Nekemte.

Weather Forecast for next day

Nov. 7, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እና የጅማ፣ ኢሉባቦርና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦኮሞ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ኖጎብ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰዮ፣ በሳለኖኖ፣ በማሻ፣ በጋምቤላ ዙሪያ እና በጎደሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሶሮ፣ በጠምባሮ፣ በአመያ፣ በሽርካ፣ በሮቤ፣ በሀዊጉዲና፣ በኩምቢ፣ በግራዋ፣ በፌዲስ፣ በባቢሌ እና በሐረር ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the south and southeast areas of our country, which are in their second rainy season, as well as in the west, southwest and east of the country. Along with this, from Oromia region West RC, Bale and East Bale, Borena, Guji and West Guji zones and Jimma, Ilubabor and Kelem Welega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dauro zones from Southwest Ethiopia region; Maokomo zone from Benshangul Gumuz region; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, South Omo and Gedo zones; Anuwak, Nuer, Itang and Majang zones from Gambella region; The Sidama region zones and the Liban, Nogob, Erer and Jarar zones of the Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in a few places.they will also get more than 30mm of heavy rain in 24 hours in Sio, Salenono, Masha, around Gambella and Godere. On the other hand, based on the intensifying weather events, Soro, Tambaro, Amaya, Shirka, Robe, Hawigudina, Kumbi, Garwa, Fedis, Babile and Harar will experience light unseasonal rain.