Daily Weather Report 24 Nov 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ቡለን፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ላይበር፣ ደባርቅ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ አለምተፈሪ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሶኮሩ፣ ኢጃጂ፣ ሐዋሳ፣ ባሌሮቤ፣ ጊኒር፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ማሻ፣ አማን፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጂንካ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሊሙገነት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the western, southwestern, and southern parts of the country. In with this, Bullen, Asossa, Gambella, Laiber, Debark, Gimbi, Nekemte, Shambu, Bedele, Alemteferi, Bure, Gore, Gatira, Chira, Sokoru, Ijaji, Hawasa, Balerobe, Ginir, Negelle, Yabelo, Moyale, Masha, Aman, Arba Minch, Mirab Abaya, Jinka and Konso received light to moderate (1-29 mm) rainfall; More than 30 mm of heavy rain was recorded over Limugenet in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦኮሞ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ኖጎብ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰዮ፣ በሳለኖኖ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በጋምቤላ ዙሪያ፣ በጎደሬ እና በመንገሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in our country's south and southeast areas, which are the second rainy season of Bega and in the west and southwest parts of the country. Along with this, from the Oromia region west Arsii, Bale and east Bale, east Borena, Guji and west Guji zones as well as Jimma, Ilubabor, Kelam and west Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Mao Komo zone; from the south Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from the Gambella region Agnuwak, Itang and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Liban, Nogob, Erer and Jarar zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in most of their areas. In addition, Sayo, Salenono, Masha, Yeki, around Gambella, Godere and Mengesh will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours.