Daily Weather Report 24 Nov 02

Weather Summary for previous day

Nov. 1, 2024

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ፤በመካከለኛው፣በምስራቅ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የመተከል ዞን፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩና ምስራቅ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሆሳዕና፣ በሐረር፣ በቢሾፍቱ፣ በኣዋሽ አርባ እና በመተሐራ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ፣ሰሜን ና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ተስተውሏል፡፡

Yesterday there was cloud cover over the southern, Central, eastern and southwestern parts of our country, which were their second rainy season of summer. At the same time, the Mekelle zone; Jimma, Ilubabor, Buno Dele, Horogudru and East Wolga, Arsi and West Arsi, Bale, West Guji, East Borena, West and East Hararge zones; Dire Dawa; Sheka, Bench Sheko and Dauro zones; Gurage, Silte and Hadiya zones; Wolayta, Gamo, Gofa and Gedeo zones and Sidama regional zones received light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Hosanna, Harar, Bishoftu, Awash Arba and Metehara. On the other hand, unseasonal rainfall was observed in the west, north, south and central Gondar, Awi Zone, west and east Gojjam, Waghemra, North Shewa, North and South Wollo Zones and west, southwest,north and east Shewa.

Weather Forecast for next day

Nov. 3, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዶሎ፣ሊበን፣ አፍደር፣ዳዋ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሞያሌ፣ በቁዳ ዱማ፣በሁዳት፣በዉጨሌ፣ በጉሚ ኢድሎ፣በኡራ፣ በሰሌኖኖ፣ በዲዱ አና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በአርማጮ፣ በደጋዳሞት፣ በወምበርማ፣ በደብረኤሊያስ፣ በአረርቲ፣በፌኖታ ሰለም፣ በአቸፈር፣ በባህርዳር፣ በይልማናደንሳ፣ በሜጫ እና በደንበጫ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud covers over the south and southeastern parts of our country which are the second rain season of Bega, and also there will be cloud accumulation over the western, central, southwestern, northwest and eastern areas of the country. In association with this, from Oromia region Bale and east Bale, east Borena, Guji and west Guji zones, as well as Jima, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, west and east Wellega zones; From the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; From Benishangul-Gumuz region, Metekel, Kamash and Assosa zones; From the Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro and Gedeo zones; From Gambella region Majang zone; Zones of Sidama region, and From Somali region Dolo, Liben, Afder, Dawa, Shebelle and Jarar zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall at many places. In addition, around Moyale, kudaDuma, udata, Wuchale, GumiAldelo, Ura, Salenono, Dedu and Masha will be received more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, it is possible that the weather events will be intensified in Armacho, Degadamot ,Wemberma, Debre Elias, Ararti, FenoteSelam,Acheffer, Bahir Dar, Yilmanadensa, Mecha and Dembecha will receive light to moderate amounts of unseasonal rainfall.