Daily Weather Report 24 Nov 01

Weather Summary for previous day

Oct. 31, 2024

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ፤ ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የፋፈን፣ ጃራር እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአይከል፣ በወሊሶ፣ በጭራ፣ በገለምሶ፣ በደሎመና፣ በሆሳዕና፣ በወራቤ፣ በምዕራብ አባያ፣ በአርባ ምንጭ እና በሽላቦ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ በምዕራብ፣ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ተስተውሏል፡፡

Yesterday there was cloud cover over the southern, southeastern, and western parts of our country, which were their second rainy season of summer. At the same time, the Mekelle and Assosa zones; Jimma and Assosa zones; Jimma and Ilubabor, Buno Dele, Kelem, Horogudru, West and East Wolga, Arsi and West Arsi, Bale, West Guji, Borena and East Borenna, West and East Hararge zones; Dire Dawa; Sheka, Bench Sheko and Dauro zones; Gurage, Silte and Hadiya zones; Wolayta, Gamo, Gofa, Gedeo and South Omo zones, Sidama regional zones and Fafen, Jarrar and Liben zones received light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Aykel, Woliso, Chira, Gemelso, Delomana, Hosanna, Werabe, Mirab Abaya, Arba Minch and Shilabo. On the other hand, unseasonal rainfall was observed in the northwest, central, south and East Tigray zones, west, north, south and central Gondar, Awi Zone, west and east Gojjam, Waghemra, North Shewa, North and South Wollo Zones and west and southwest Shewa.

Weather Forecast for next day

Nov. 2, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በደቡብ አቸፈር፣ በጎቡ ሰዮ፣ በባኮቲቤ፣ በሚዳኬኝ፣ በሰተማ፣ በጌራ፣ በደዶ፣ በቀርሳ፣ በማንቾ፣ በኦሞበያም፣ በሶኮሩ፣ በሻሸመኔ፣ በሲራሮ፣ በአርሲነገሌ፣ በየም ልዩ ዞን፣ በለሞ፣ በጊቤ፣ በሚሻ፣ በሳርኩራ፣ በሶሮ፣ በጠምባሮ፣ በካቻብራ፣ በቦሎቦምቤ፣ በተርጫ፣ በዲሳ፣ በኮንታ ኮይሻ፣ በሳይለም፣ በገሻ፣ በጊምቦ፣ በቱሎ፣ በማሻ፣ በወራ እና በሐዋሳ ዙሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በደባርቅ፣ በአርማጮ፣ በአቸፈር፣ በደምቢያ፣ በአለፋ፣ በጣቁሳ፣ በደራ፣ በባህርዳር፣ በይልማናደንሳ፣ በሜጫ፣ በደንበጫ፣ በደጋዳሞት፣ በወምበርማ፣ በደብረኤሊያስ፣ በአረርቲ፣ በግንደበረት፣ በጀልዱ፣ በአምቦ፣ በደንዲ፣ በሜታሮቢ፣ በአመያ፣ በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በቶሌ፣ በቡታጂራ፣ በሰበታሓዋስ፣ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ፣ በአዳማ፣ በአዳሚቱሉ፣ በዱጉዳ፣ በሙኔሳ፣ በሮቤ፣ በመርቲ፣ በአሰኮ፣ በአንቻር፣ በጎሎልቻ፣ በጠና፣ በዶዶታ፣ በሴሩ፣ በጮሌ፣ በቦኬ፣ በቡርቃ፣ በግራዋ፣ በመሰላ፣ በፌዲስ፣ በኩርፋጨሌ፣ በሐሮማያ በሐረር፣ በኮራን፣ በቸሃ፣ በቀበና እና በስልጤከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበስብ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡

Tomorrow there will be cloud covers over the south and southeastern aparts of our country which are the second rain season of Bega, and also there will be cloud accumulation over the western, central, southwestern, northwest and eastern areas of the country. In association with this, from Oromia region west Arsi, Bale and east Bale, east Borena, Guji and west Guji zones, as well as Jima, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, west and east Wellega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones from the Southwest Ethiopia region; From Benishangul-Gumuz region, the Metekel, Kamash and Assosa zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro and Gedeo zones; from Gambella region, Agnwuak and Majang zones; the zones of Sidama region, and from Somali region Liben, Dawa, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Dolo, Erer and Jarrar zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall at many places. In addition, around Jawi, Dangla, South Achefer, Gobu Seyo, Bako Tibe, Mida Kegne, Satema, Gera, Dedo, Kersa, Mancho, Omobeyam, Sokoru, Shashemene, Siraro, Arsi negele, Yem Special zone, Lemo, Gibe, Misha, Sarku ura, Soro, Tembaro, Kachabra, Bolobombe, Tercha, Disa, Konta Koisha, Sailum, Gesha, Gimbo, Tulo, Masha, Wera and Hawassa will be received more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours. On the other hand, based on the intensifying weather events, it is possible that the weather events will be intensified in Debark, Armacho, Acheffer, Dembia, Alfa, Takusa, Dera, Bahir Dar, Yilmanadensa, Mecha, Dembecha, Degadamot, Wemberma, Debre Elias, Ararti, Gendebret, Jeldu, Ambo, Dundee, Metarobi, Amaya, Wente, Woliso, Tole, Butajira, Sebetawas, Addis Ababa, Bischoftu, Adama, Adamitulu, Duguda, Munesa, Robe, Merti, Asko, Anchar, Gololcha, Tata, Dodota, Seru, Chole, Boke, Burqa, Grawa, Mesela, Fedis, Kurfakele, Haramaya, Harar, Koran, Cheha, Kebena and Silte will receive light to moderate amounts of unseasonal rainfall. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute suggests that the community harvest mature crops.