Daily Weather Report 24 May 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ደራሼ እና አማሮ ዞኖች ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በወላይታ፣ ሳዉላ ፣ ዲላ እና አሊያ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቦባቸዋል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in North West, North East, West, South, South and West areas of the country. Thus, from the Amhara region, North, South and Central Gondar, North Showa, West and East Gojam, North and South Wolo zones; From Oromia region Jimma, Ilubabor, North and West Showa, East, West, Horo Gudruna, Kelem Wollega, Guji and West Guji zones; Harar; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region Metekel, Asosa, Mao Komo zones; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Derashe and Amaro zones of Southern Ethiopia region and zones of, Sidama region; From the central region of Ethiopia, Gurage, Silte, Hadia, Kebatama and Tembaro zones received light to moderate rainfall, and heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Wolayta, Sawula, Dila and Aliya.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይበልጥ ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ቄለም ወለጋ፣ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ሸካ ፣ከፋ እና በፋፈን ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow the weather events favorable for the formation of rain will continue to strengthen the cloud cover and accumulation in the northwest, west, south, southwest and east areas of our country. Along with this, Tigray region the western, north western and central zones; from Amhara region North, South and Central Gondar, Awi, West and East Gojam zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Welega, Southwest, North and West Showa, Borena, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Harar; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region Metekel, Asosa, Mao Komo zones; from the Gambella region Nuer, Itang, Anuwak and Majang zones ; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; From Central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Kambata and Tembaro zones; All zones from Sidama region; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones; Fafen, Jarar, Erer, Nogob, Korahe zones of Somali region will have light to moderate rainfall in many places. In addition, a few areas such as Plantation, Asosa, Mao Komo, Kelem Wollega, Ilubabor, Buno Dele, Jimma, Sheka, Kefa and Fafen zones will experience heavy rains of more than 30 mm in 24 hours.