Daily Weather Report 24 June 2024

Weather Summary for previous day

June 23, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተጠናከረ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን፤ ከአፋር ክልል ጋቢ ዞን፤ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በተጨማሪም በመተሀራ፣ በነቀምቴ፣ በወገልጤና፣ በካቺሴ፣ በፊቼ፣ በኮምቦልቻ (ምስራቅ ሀረርጌ)፣ በባህር ዳር እና በኮምቦልቻ አካባቢዎች ላይ ደግሞ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had intensified cloud cover over western, northeastern, eastern, southern, and central areas of the country. In connection with this, At the same time, the Central and East Zones of Tigray Region, from Amhara region north and central Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Awi zones; from Oromia region Jimma, Buno Bedele, Horogudru, west and east Wolga, west, southwest, east and north Shewa, east and west Hararge, Arsi and west Arsi zones; Benishangul-Gumuz region, Asosa zone, southwest Ethiopia region, Dauro and Bench Sheko zones; Gedeo zone of southern Ethiopia region; Somali region Fafen zone; Afar region, Gabi zone, Harar, Dire Dawa, and Addis Ababa had light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in the areas of Metehara, Nekemte, Wogltena, Kachise, Fiche, Kombolcha (East Hararge), Bahir Dar and Combolcha.

Weather Forecast for next day

June 25, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፤ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ ፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦኮሞ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ እና ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሃቲና ፋንቲ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ጅማ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

For the next day, Weather events favorable for winter rainfall will intensify over the northwest, central, northeast, east, south and southwest parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, North and South Wollo, North Shewa, Oromia Special zone and Waghemra zones; Oromia region: Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east Wolga, southwest, north, east and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale and west Harerge zones; Addis Ababa; from Benishangul-Gumuz region Maokomo zone; from Gambella region Majang and Agnuwak zones; west Ethiopia region: Sheka, Kefa, Bench Sheko, Dauro and Konta zones; Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kembatana Tembaro zones; all zones of Sidama region; from Southern Ethiopia region Wolayta and Gedeo zones; and from Afar region, the Kilbeti, Aussie, Gabi, Hati and Fanti zones will receive light to moderate amounts of rainfall at many of their locations. In addition, north and south Gondar, west Gojjam, Waghemra, Jimma, west and north Shewa zones will receive heavy rainfall within 24 hours.