Daily Weather Report 24 July 18

Weather Summary for previous day

July 17, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በባቱ፣ በፉኝዶ እና በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the northwest, west, central, south, northeast and east parts of the country. In association with this, northwest, central and southeast zones of the Tigray region; from Amhara region north and south Gondar, east and west Gojjam, Awi, north and south Wollo, Waghemra and north Shewa zones; Assosa zone from Benishangul-Gumuz region; from Oromia region Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, west and east Wollga, Horogudru Wollga, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, Guji, east Hararge zones; Addis Ababa, from Central Ethiopia region: Gurage, Hadia and Silte Zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Kefa, Benchi Sheko and Dauro Zones; from South Ethiopia region Gamo, Gofa, Wolayta, Konso and Gedeo zones, and from Gambella region Agnwak zone received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Batu, Fugnudo and Arjo.

Weather Forecast for next day

July 19, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ ዳዉሮ፣ኮንታ፣ ደቡብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ማጃንግ እና ጉራጌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈንና ሲቲ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the weather forecast information indicates that weather events favorable to the formation of Kiremt rainfall will intensify. In association with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo Ethnic Special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Ausi and Hati zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Mao Como, Asossa and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east and west Wollga, Horogudru Wollga, Kelem Wollga, southwest, east, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; from Gambella region Agnwuak, Majang and Itang zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko Dauro, south Omo, Konta and Kefa zones; from the Central Ethiopia region, the zones of Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro, all zones from the Sidama region and from will receive light to moderate amounts of rainfall at many of their locations. In addition, central and south Tigray, west, central and south Gondar, north, west, east and southwest Shewa, Addis Ababa, Arsi, Jimma and east Wollga, Kamash, Gurage, Silte, Hadia, Sheka and Bench Sheko zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Southern Ethiopia region Gamo, Gofa, Wolayta and Gedeo zones, Harar, Dire Dawa, west and east Hararge, Bale, Fafen and Siti zones of Somali region in a few places will receive light amounts of rain.