Daily Weather Report 24 July 17

Weather Summary for previous day

July 16, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞናኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን እና ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ሀቲ እና ጋቢ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዳልፋጌ፣ በአፅቢ፣ በሐረር፣ በአይራ፣ በሰመራ፣ በጅማ፣ በመተሐራ፣ በነቀምቴ፣ በኮምቦልቻ፣ በአምባ ማርያም፣ በካራሚሌ እና በባቢሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover and accumulation over areas of the northwest, west, central, south, northeast and east of the country. In association with this, northwest, central, east and southeast zones of the Tigray region; from Amhara region north, central and south, Gondar, east Gojjam, Awi, north and south Wollo and north Shewa zones; Assosa zone from Benishangul-Gumuz region; from Oromia region Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, west and east Wollga, Horogudru Wollga, west, east and north Shewa, Arsi, Bale, Guji, east and west Hararge Zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa; from Central Ethiopia region: Gurage, Hadia and Silte Zones; from Southwest Ethiopia region Dauro Zone; from South Ethiopia region Gamo, Gofa, South Omo and Gedeo zones, from the Somali region Fafen zone and from Afar region Aussie, Hati and Gabi zones received light to moderate amounts of rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Dalfage, Atsbi, Harar, Aira, Semera, Jimma, Tercha, Nekemte, Kombolcha, Amba Mariyam, Karamile and Babile.

Weather Forecast for next day

July 18, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦ ኮሞ፣አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ ዳዉሮ፣ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ጎፋ፣ወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ፣ ምዕራብ ፣ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ አርሲ፣ጅማ እና ምስራቅ ወለጋ፣ካማሽ፣ ጉራጌ ፣ስልጤ፣ሀድያ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፣ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ፣ ደራሼ እና አማሮ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ ባሌ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈንና ሲቲ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, weather events favorable to the formation of Kiremt rainfall will continue to intensify over the southwest, west, north, northeast, central, east and southern parts of the country. In association with this, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; from Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo Ethnic Special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Ausi and Hati zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Mao Como, Asossa and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east and west Wollga, Horogudru Wolga, Kelem Wollga, southwest, east, north and west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; from Gambella region Anwuak Majang, Nuer and Itang zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko Dauro, Konta and Kefa zones; from the Central Ethiopia region, the zones of Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro, all zones from the Sidama region and from Southern Ethiopia region Gamo, Gofa, Wolayta and Gedeo zones will receive light to moderate amounts of rainfall at many of their locations. In addition, central and south Tigray, west, central and south Gondar, north, west, east and southwest Shewa, Addis Ababa, Arsi, Jimma and east Wollga, Kamash, Gurage, Silte, Hadia, Sheka and Bench Sheko zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the occasional weather events, the Anuak Zone of Gambella region, South Omo, Derashe and Amaro Zones, Harar, Dire Dawa, west and east Hararge, Bale, Fafen and Siti zones of Somali region in a few places will receive light amounts of rain.