Daily Weather Report 24 July 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ጉጂ፣ቦረና፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ አዲስ አበባ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤና ሀድያ ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ እና ጎፋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በባህር ዳር፣ ዳንግላ፣ ላይበር፣ ደ/ብርሃን፣ አ/አበባ፣ ሆሳዕና፣ እምድብር፣ ቡኢ፣ ቢሾፍቱ እና ሾላ ገበያ ላይ ከ30 ሚ.ሜ ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, they had strong cloud accumulation in the northwest, northeast, central, south, and eastern parts of the country. In connection with this, the central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; North, Central and South Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, Waghemra and North Showa zones of Amhara Region; From the Oromia region of Jimma, Buno Bedele, Horo Gudru Wollega, East and West Showa, RC, Guji, Borena, West Hararge zones; Harar; Dire Dawa; Addis Ababa; Gurage, Silete and Hadia zones from central Ethiopia region, Wolayta and Gofa zones from southern Ethiopia region; Zones of Sidama region received light to moderate rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የምዕራብ አጋማሽ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ እና የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ፣ ምዕራብ ፣ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ኑዌር፣ ሆሮጉድሩ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉራጌ ፣ስልጤ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ፣ ደራሼ እና ወላይታ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከአፋር ክልል ፋንቲ፣ ሀቲ፣ ቂልበቲ፣ አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፣ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ፤ ባሌ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Heavy and widespread cloud cover will prevail over the western, northeastern, central, eastern and southern parts of the country, which will benefit from Kiremt rains. In addition, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, Oromo Special Zone, North Showa and Waghemra Zones of Amhara region; Plantation, Asosa and Kamash zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East and West Welega, Horo Gudru Welega, Kelem Welega, Southwest, East, North and West Showa, RC and West RC zones; Addis Ababa; Anuwak, Majang, Nuer and Itang zones from Gambella region; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia region; From the central region of Ethiopia, Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kambata and Tambaro zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, North West, Central and South Tigray, West, Central and South Gondar, North, North West, East and West Showa, Addis Ababa, Nuer, Horo Gudru and East Wollega, Gurage, Silte, Sheka and Bench Sheko zones will receive more than 30 mm in 24 hours. You will get heavy amount of rain above. On the other hand, based on the occasional intensifying weather events, Gedeo, Derashe and Wolayta zones of Southern Ethiopia region; Sidama Region Zones, Fanti, Hatti, Kilbeti, Awusi and Gabi Zones of Afar Region, Harar; Dredawa, West and East Hararge, Guji; Bale; Our numerical forecast data indicates that the Fafen zone of the Somali region will receive light amounts of rain in a few places.