Daily Weather Report 24 July 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ጉጂ፣ቦረና፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤና ሀድያ ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ እና ጎፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአልጌ፣ ነቀምቴ፣ ቻግኒ፣ አማን፣ ሻሁራ እና ዳንግላ ላይ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, they had cloud cover and accumulation in the North-West, Central, South, North-East and East regions of the country. In connection with this, from Amhara region North, Central and South Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo and North Showa zones; From the Oromia region of Jimma, Buno Bedele, Horo Gudru Wollega, East and West Showa, RC, Guji, Borena, West Hararge zones; Addis Ababa; From the central Ethiopian region of Silte and Hadya zones, from the southern Ethiopian region of Wolayta and Gofa zones; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; Zones of Sidama region received light to moderate rainfall. Alge, Nekemte, Chagni, Aman, Shahura and Dangla also received heavy rainfall of more than 30 mm.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የምዕራብ አጋማሽ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ እና የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ፣ ምዕራብ ፣ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ኑዌር፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ አሶሳ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ እና ወላይታ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከአፋር ክልል ፋንቲ፣ ሀቲ እና ጋቢ ዞኖች፣ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ፤ ባሌ፤ ቦረና፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ቆራሄ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow the Weather conditions favorable for the formation of winter rains tomorrow will have strong and widespread cloud cover and accumulation over the western, northeastern, central, eastern and southern parts of the country. In addition, the central, northwest, southeast, south and east zones of the Tigray region; North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, Oromo Special Zone, North Showa and Waghemra Zones of Amhara Region; Metekel, Asosa and Kamash zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East and West Welega, Horo Gudru Welega, Kelem Welega, Southwest, East, North and West Showa, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; Anuwak, Majang, Nuer and Itang zones from Gambella region; From the Sheka, Bench Sheko and Kefa zones of South West Ethiopia; From the central region of Ethiopia, Gurage, Silte, Halaba, Hadia, M Special Zone, Kambata and Tembaro zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, North West, Central and South Tigray, West, Central and South Gondar, North and West Showa, Addis Ababa, Nuer, West Arsi, Kelem and West Wollega, Assosa, Gurage and Silte zones with a heavy amount of more than 30 mm in 24 hours. They get rain. On the other hand, Gedeo and Wolayta zones of Southern Ethiopia region; Sidama Region Zones, Fanti, Hatti and Gabi Zones of Afar Region, Harar; Dire Dawa, West and East Hararge, Guji; Bale; Borena. Fafen and Korahe zones of Somali region will receive light rain at few places.