Daily Weather Report 24 Dec 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በመሆኑም በአዲግራት 4.0፣ በማይጨው 4.0፣ በወገልጤና 0.6፣ በባቲ 4.2፣ በደብረወርቅ 4.2፣ በአለምከተማ 4.2፣ በእንዋሪ 4.5፣ በደብረብርሀን 4.0፣ በሾላ ገበያ 3.0፣ በፍቼ 3.5፣ በቢሾፍቱ 4.0፣ በቡኢ 1.0፣ በአርሲ ሮቤ 3.0፣ በሐሮማያ 2.8 እና በጅግጅጋ 1.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, the dry, sunny and windy weather condition was observed in the north, northeast, central, southern highlands and eastern parts of our country. Accordingly, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Adigrat 4.0, Michew 4.0, WegelTena 0.6, Bati 4.2, Debrework 4.2, Alemketema 4.2, Enwari 4.5, Debrebirhan 4.0, Sholagebeya 3.0, Fiche 3.5, Bishoftu 4.0, Bui 1.0, Arsi Robe 3.0, Haramaya 2.8 and Jigjiga 1.0. On the other hand, there was cloud coverage in the southwestern parts of our country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲግራት፣ በደባርቅ፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በባሌ ሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the next day, the Bega dry, sunny and windy weather condition will be observed across most parts of our country. Accordingly, the forecast information indicates that the daily minimum temperature will be below 5°C in Adigrat, Debark, WegelTena, Bati, Amba Mariam, Mehalmeda, Debre Beirhan, Enwari, Alemketema, Sholagebeya, Arsi Robe, Bale Robe, Haramaya and Jigjiga, and the nighttime and early morning coldness will continue. On the other hand, there will be occasional cloud cover over the southwest, northeast and eastern parts of the country.