Daily Weather Report 24 Dec 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማይጨው 4.5፣ በወገልጤና 1.8፣ በደብረወርቅ 4.2፣ በአለምከተማ 3.0፣ በእነዋሪ 4.0፣ በመሀልሜዳ 0.5፣ በደብረብርሀን -1.0፣ በሾላገበያ 2.0፣ በፍቼ 3.5፣ በቢሾፍቱ 2.0፣ በቡኢ 2.0፣ በእምድብር 4.8፣ በአርሲሮቤ 2.5፣ በባሌሮቤ 4.4፣ በሐሮማያ 2.0 እና በጅግጅጋ 0.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather was observed across most parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Maichew 4.5, Wegeltena 1.8, Debrework 4.2, Alemketema 3.0, Enewari 4.0, Mehalmeda 0.5, Debrebrehan -1.0, Sholagebeya 2.0, Fiche 3.5, Bishoftu 2.0, Bui 2.0, Emdibir 4.8, Arsirobe 2.5, Balerobe 4.4, Haromaya 2.0 and Jijiga 0.2.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በአምባማሪያም፣ በኮምቦልቻ፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በአደሌ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ፣ በእምድብር እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the Bega dry, sunny, and windy weather will prevail over most parts of our country. Accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Debark, Ambamariam, Kombolcha, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Adele, Balerobe, Haromaya, Emdibir and Jijiga. On the other hand, there will be occasional cloud coverage in the south, southwest, and northeast parts of the country.