Daily Weather Report 24 Dec 29

Weather Summary for previous day

Dec. 28, 2024

በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በፍቼ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በአደሌ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቡኢ፣ በሀሮማያ፣በደብረ ብርሀን፣ በማይጨዉ፣ በአፅቢ፣ በአድግራት፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀል ሜዳ፣ በወራ ኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በኮምቦልቻ፣ በወገል ጤና፣ በደባርቅ፣ በእንድብር እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow, the Bega’s dry, sunny, and windy weather will be observed in the northeast, north, northwest, central, Southern Highlands, and eastern parts of our country. Therefore, the minimum temperature of the day will be below 5°C in Fiche, Adelle, Bishoftu, Arsi Robe, Bale Robe, Bui, Haramaya,Debre Berhan, Maichew,Atsebi, Adgrat, Shola Gebeya, Enwari, Mehal Meda, Wera Ilu, Amba Maryam, Combolcha, Wegeltaena, Debark, Endibir and Jigjiga, and the night and morning time coldness will continue to be the same way.

Weather Forecast for next day

Dec. 30, 2024

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአምባ ማርያም 4.5፣ በኮምቦልቻ 3.2፣ በቢሾፍቱ 4.1፣ በቡኢ 3.0፣ አርሲ ሮቤ 3.5 እና በባሌ ሮቤ 3.8 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፉኚዶ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, over the northeastern, northern, northwestern, central, southern high ground and eastern parts of the country the Bega dry, sunny, and windy weather condition was observed. In this regard, the daily minimum temperature were recorded below 5°C in Amba Maryam 4.5, Combolcha 3.2, Bishoftu 4.1, Bui 3.0, Arsi Robe 3.5 and Bale Rob 3.8.