Daily Weather Report 24 Dec 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሾላገበያ 3.5፣ በሐሮማያ 4.6 እና በጅግጅጋ 3.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎሬ፣ በነቀምቴ፣ በፉኝዶ እና በሳዉላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ዝናብ ያገኙ ሲሆን በማሻ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, over the northern, northwestern, central, northeastern, and eastern parts of the country the Bega dry, sunny, and windy weather condition was observed. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Sholagebeya 3.5, Haromaya 4.6 and Jijiga 3.2. On the other hand, there was cloud coverage over the western, southwestern, and southern parts of our country. In line with this, Gore, Nekemte, Fugnido, and Sawula received light to moderate rainfall, while heavy rain of more than 30 mm was recorded in Masha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ስለሆነም በአይደር፣ በአፅቢ፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በአደሌ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ከፋ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will be observed in most parts of our country. Thus, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Aider, Atsebi, Debark, Dangila, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Adele, Balerobe, Haromaya and Jijiga. In contrast, the southwestern and southern areas of the country will experience cloud coverage; with light rainfall expected in a few places of Ilubabor, Sheka, and Kefa and Majang zones.