Daily Weather Report 24 Dec 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያይዞ በሾላ ገበያ 3.3፣ በሐሮማያ 4.6 እና በጅግጅጋ 3.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፉኚዶ፣ በጭራ እና በጋቲራ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northern, north eastern, central and eastern regions of our country experienced dry, sunny and windy weather conditions. In line with this, the minimum temperature of the day was recorded below 50C in Shola Gebeya 3.3, Haromaya 4.6 and Jigjiga 3.2. On the other hand, there was cloud coverage in the southern and southwestern parts of our country. In association with this, light rain was recorded in Fugnido, Chira and Gatira.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸዉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በማሻ፣ ቴፒ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ አኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ምዕራብ አርሲ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ የገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛ እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀልሜዳ፣ በወረ ኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በወገል ጤና፣ በአዲግራት፣ በሐሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በአደሌ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቡኢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For tomorrow, there will be cloud coverage over the southern and southwestern regions of our country, and in connection with this, Masha, Tepi, Sheka, Bench Sheko, West Omo, Kefa, Konta, Jimma, Ilubabor, Agnuak, Majang, Gofa, Basketo, West Arsi and Sidama regional zones will experience light rain. On the other hand, the northern, north eastern, north western, central and eastern regions of our country will experience dry, sunny and windy weather conditions. Therefore, numerical forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 50C in Debre Berhan, Shola Gebeya, Enwari, Mehalmeda, Were Ilu, Amba Mariam, Wegel Tena, Adigrat, Haromaya, Arsi Robe, Adele, Bishoftu, Bale Robe, Bui and Jigjiga.