Daily Weather Report 24 Dec 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ 4.5፣ በዳንግላ 4.5፣ በአምባማሪያም 4.4፣ በሾላገበያ 4.0፣ በሐሮማያ 4.8 እና በጅግጅጋ 3.4 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቴፕ እና በተርጫ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, over the northern, northwestern, central, northeastern and eastern parts of the country the Bega dry, sunny and windy weather condition was observed. As a result, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Debark 4.5, Dangila 4.5, Ambamariam 4.4, Sholagebeya 4.0, Haromaya 4.8 and Jijiga 3.4. On the other hand, there was cloud coverage over the southwestern parts of our country. In line with this, light rainfall was recorded over Tepi and Tercha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በአዴት፣ በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጅማ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳዉሮ፣ አኙዋክ፣ ማጃንግ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌድኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny and windy weather will prevail over the north, northeast, northwest, central and eastern parts of the country. Thus, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Maichew, Debark, Dangila, Adet, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Haromaya and Jijiga. Conversely, there will be cloud coverage in the southwest and southern area of our country; with light rain anticipated in the Jimma, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, Dawuro, Agnuwak, Majang, Gofa, Basketo, Gedeo and Sidama region zones.