Daily Weather Report 24 Dec 24

Weather Summary for previous day

Dec. 23, 2024

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያይዘ በዳንግላ 5.0፣ በአምባ ማርያም 4.5፣ በመሀል መዳ 2.6፣ በደብረ ብርሀን 4.2፣ ወገልጤና 5.0፣ በሾላ ገበያ 3.0፣ በሐሮማያ 3.8፣ በጅግጅጋ 2.4፣ በቡኢ 4.4፣ በቢሾፍቱ 5.0 እና በአርሲ ሮቤ 3.5 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 0 C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the dry, sunny and windy weather of the Bega was observed in the northwest, northeast, central and eastern areas. In addition, in Dangla 5.0, in Amba Maryam 4.5, in Mehal Meda 2.6, in Debre Berhan 4.2, in Wegeltena 5.0, in Shola Gebeya 3.0, in Haromaya. 3.8, in Jigjiga 2.4, Bui 4.4, Bishoftu 5.0 and Arsi Robe 3.5 recorded the minimum temperature of the day below 5°C.

Weather Forecast for next day

Dec. 25, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን ፤ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ጎፋ፣ ወላይታ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀልሜዳ፣ በወረኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በኮምቦልቻ፣ በወገል ጤና እና በፍቼ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, the second rainy season of the Bega, there will be cloud cover in the south and southwest areas of the country. Sheka, Bench Sheko, West Omo, Dawuro, Konta and Kefa zones from South West Ethiopia region; The Gamo, Gofa, Wolayta, Derashe, Konso, South Omo and Gedo zones of Southern Ethiopia region and the Sidama region zones will receive less rainfall. On the other hand, the north-eastern, central and eastern regions of our country experience dry, sunny and windy Bega weather. Therefore, numerical forecasts indicate that the minimum temperature of the day will be below 5°C in Debre Berhan, Shola Gebeya, Anwari, Malmeda, Wareilu, Amba Maryam, Kombolcha, Wegel Tena and Fiche.