Daily Weather Report 24 Dec 23

Weather Summary for previous day

Dec. 22, 2024

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በዳንግላ 4.5፣ በደባርቅ 4.5፣ በመሀል ሜዳ 3.0፣ በሾላ ገበያ 1.2፣ በአርሲ ሮቤ 3.0፣ በቢሾፍቱ 4.2፣ በሐሮማያ 2.5፣ በቡኢ 3.6 እና በጅግጅጋ 2.4 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን፤ በማጂ፣ በጅንካ እና በሳውላ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather was observed in the northeast, northwest, central and east parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature was recorded below 5°C in the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Dangla 4.5, Debark 4.5, Mehal Meda 3.0, Shola Gebeya 1.2, Arsi Robe 3.0, Bischoftu 4.2, Haramaya 2.5, Bui 3.6 and Jigjiga 2.4. On the other hand, they had cloud cover in the southwest and southern Ethiopia and then rainfall was recorded in Maji, Jinka, and Sawla.

Weather Forecast for next day

Dec. 24, 2024

በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በወገል ጤና፣ በአምባ ማርያም፣ በመሀልሜዳ፣ በእንዋሪ፣ በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በቢሾፍቱ እና በቡኢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the dry, sunny and windy weather of the Bega will be observed in the northeastern, central and eastern parts of our country. In line with this, that the daily minimum temperature will be below 5°C in WegelTena, Amba Maryam, Malmeda, Enwari, Debre Birhan, Shola Gebeya, Bischoftu and Bui. On the other hand, there will be cloud cover in the south and southwest parts of the country. Along with this, from Oromia region west Arsi, Bale, Borena, Guji and west Guji and Jimma zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawro, west Omo, Konta and Kefa zones; from South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo and Gedo zones and Sidama region will receive light rainfall.