Daily Weather Report 24 Dec 22

Weather Summary for previous day

Dec. 21, 2024

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘ በዳንግላ 3.8፣ በመሀል ሜዳ 4.8፣ በወገልጤና 4.5፣ በሾላ ገበያ 2.0 በአርሲ ሮቤ 3.0፣ በቢሾፍቱ 4.2 እና በቡኢ 3.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ደቡብ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአርባ ምንጭ፣ በምዕራብ አበያ እና ሳውላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather was observed in the northeast, central and east parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature was recorded below 5oC in Dangla 3.8, Mehalmeda 4.8, Shola Gebeya 2.0 Arsi Robe 3.0, Bishoftu 4.2 and Bui 3.6. On the other hand, they had cloud cover in southern parts of Ethiopia. In association with this, light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall were recorded in Arba Minch, Mirab Abaya and Sawla.

Weather Forecast for next day

Dec. 23, 2024

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በወገል ጤና፣ በአምባ ማርያም፣ በመሀልሜዳ፣ በእንዋሪ፣ በደብረ ብርሀን እና በሾላ ገበያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover over the southwest and south parts of our country. In association with this, from Oromia region west Arsi, Bale, Borena and East Borena, Guji and west Guji and Jimma zones; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawro, west Omo, Konta and Kefa zones; from Central Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, South Omo and Gedeo zones; from Central Ethiopia region Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; Sidama regional Zones and from Somali region Dawa zone will receive rainfall light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall. On the other hand, the northeastern, central and eastern areas of our country experience dry, sunny and windy Bega weather conditions. Along with this, the daily minimum temperature will be below 5°C in Wegel Tena, Amba Mariyam, Mehalmeda, Enwari, Debre Birhan and Shola Gebeya.