Daily Weather Report 24 Dec 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘ በዳንግላ 4.0፣ በአምባ ማርያም 4.8፣ በመሀል መዳ 4.0፣ በደብረ ብርሀን 4.4፣ በወገልጤና 3.5፣ በሾላ ገበያ 2.0 እና በቡኢ 4.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5OC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአርባ ምንጭ፣ በጂንካ እና በሳውላ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather was observed in the northeast, central and east parts of the country. In association with this, the daily minimum temperature was recorded below 5oC in Dangla 4.0, Amba Mariam 4.8, Mehalmeda 4.0, Debre Birhan 4.4, Wegeltena 3.5, Shola Gebeya 2.0 and Bui 4.0. On the other hand, they had cloud cover in southern Ethiopia. In association with this, light amounts of rainfall were recorded in Arba Minch, Jinka and Sawla.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ፣ ጅማ እና ኢሉባበቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በወገል ጤና፣ በአምባ ማርያም፣ በመሀልሜዳ፣ በእንዋሪ፣ በአለም ከተማ፣ በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በፍቼ እና በቡኢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southwest, south and southeast areas of our country. In this regard, Oromia region west Arsi, Bale, Borena, Guji, Jimma and Ilubabebor zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Dawro, Konta and Kefa zones; from south Ethiopia region Gofa, Wolaita, Basketo, South Omo and Gideo zones; the zones of the Sidama region, and from Somali region Dawa and Afder zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. On the other hand, the northeastern, central and eastern areas of our country experience dry, sunny and windy Bega weather conditions. Along with this, numerical forecast data show that the daily minimum temperature will be below 5°C in Wegel Tena, Amba Mariyam, Mehalmeda, Enwari, Alem Ketema, Debre Birhan, Shola Gebeya, Fiche and Bui.