Daily Weather Report 24 Dec 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያይዘ በዳንግላ 4.2፣ በአምባ ማርያም 4.2፣ በመሀል መዳ 3.8፣ በእንዋሪ 5.0፣ በደብረ ብርሀን 3.4፣ አለም ከተማ 4.8፣ ወገልጤና 3.5፣ በሾላ ገበያ 2.4፣ በሐሮማያ 0.2፣ በጅግጅጋ 0.0፣ በቡኢ 2.8 እና በአርሲ ሮቤ 2.5 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 0 C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the dry, sunny and windy weather of the Bega was observed in the northeast, central and eastern areas. In addition, in Dangla 4.2, Amba Maryam 4.2, Mehal Meda 3.8, Anwari 5.0, Debre Berhan 3.4, Alem City 4.8, Wegeltena 3.5, Shola. Market 2.4, 0.2 in Haromaya, 0.0 in Jigjiga, 2.8 in Bui and 2.5 in Arsi Robe, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ፣ ጋሞ፣ጎፋ፣ ወላይታ፣ደራሼ፣ ኮንሶ እና ጌድኦ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ስለሆነም በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀልሜዳ፣ በወረኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በኮምቦልቻ፣ በወገል ጤና እና በፍቼ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud cover in the south and southeast areas of the country, which will be their second rainy season of the Bega. Along with this, from Oromia region West Arsi, Bale East Bale, Borena and East Borena, Guji West Guji and Jimma zones; Sheka, Bench Sheko, West Omo, Konta and Kefa zones from South West Ethiopia region; From South Ethiopia region of Amaro, Gamo, Gofa, Wolayta, Derashe, Konso and Gedo zones of Sidama region and Dawa and Afder zones of Somali region receive light to moderate rainfall (1-29 mm). On the other hand, the northeastern, central and eastern regions of our country experience dry, sunny and windy Bega weather. Therefore, numerical forecasts indicate that the minimum temperature of the day will be below 5°C in Debre Berhan, Shola Market, Enewari, Malmeda, Wareilu, Amba Maryam, Kombolcha, Wegel Health and Fiche.