Daily Weather Report 24 Dec 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በወገልጤና 3.0፣ በአምባማሪያም 4.0፣ በባቲ 4.8፣ በመሀልመዳ 4.0፣ በአለምከተማ 4.0፣ በደብረብርሀን 0.8፣ በሾላገበያ 3.0፣ በቢሾፍቱ 2.0፣ በቡኢ 2.0፣ በአርሲሮቤ 3.5፣ በሐሮማያ 1.6 እና በጅግጅጋ 4.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather condition was observed in all parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Wegeltena 3.0, Ambamariam 4.0, Bati 4.8, Mehalmeda 4.0, Alemketema 4.0, Debrebrehan 0.8, Sholagebeya 3.0, Bishoftu 2.0, Bui 2.0, Arsirobe 3.5, Haromaya 1.6 and Jijiga 4.6.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny and windy weather condition will prevail across most parts of our country. Accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Debark, Wegeltena, Bati, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jijiga, with continued cold condition during the night and morning. Conversely, there will be cloud coverage in the country's southwestern areas.