Daily Weather Report 24 Dec 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በአብዛኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአድግራት 4.0፣ አምባ ማርያም 4.0፣ መሀል መዳ 4.2፣ አለም ከተማ 4.0፣ እንዋሪ 4.5፣ ደብረ ብርሀን 2.2፣ ፍቼ 4.0፣ ሐሮማያ 1.4፣ ቢሾፍቱ 2.4፣ ቡኢ 2.4፣ አርሲ ሮቤ 3.0፣ ባሌ ሮቤ 4.8 እና ጅግጅጋ 1.4 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ የደመና ሽፋን የነበረ ሲሆን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, most parts of our country experienced Bega’s dry, sunny, and windy weather conditions. In association with this, the minimum daily temperatures were recorded below 5°C in Adigrat 4.0, Amba Mariam 4.0, Mehal Meda 4.2, Enwari 4.5, Debre Berhan 2.2, Fiche 4.0, Haromaya 1.4, Bishoftu 2.4, Bui 2.4, Arsi Robe 3.0, Bale Robe 4.8, and Jigjiga 1.4. On the other hand, there was cloud cover in Gambella and light amounts of rain were recorded.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በማይጨዉ፣ በአፅቢ፣ በአድግራት፣ በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀል ሜዳ፣ በወራ ኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በኮምቦልቻ፣ በወገል ጤና፣ በደባርቅ፣ በእንድብር፣ በፍቼ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በአደሌ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቡኢ፣ በሀሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል የደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For tomorrow, the Bega’s dry, sunny, and windy weather will be observed in the northeast, north, northwest, central, Southern Highlands, and eastern parts of our country. Therefore, the minimum temperature of the day will be below 5°C in Ethiopia, Atsebi, Adgrat, Debre Berhan, Shola Gebeya, Enwari, Mehal Meda, Wera Ilu, Amba Maryam, Combolcha, Wegeltaena, Debark, Endibir, Fiche, Adelle, Bishoftu, Arsi Robe, Bale Robe, Bui, Haramaya, and Jigjiga, and the nighttime and morning coldness will continue to be the same. On the other hand, there will be cloud cover over the south and southwest parts of our country.