Daily Weather Report 24 Dec 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ 4.5፣ በወገልጤና 1.8፣ በአምባማሪያም 4.0፣ በመሀልመዳ 1.0፣ በአለምከተማ 3.8፣ በእነዋሪ 2.5፣ በደብረብርሀን 2.6፣ በቢሾፍቱ 1.2፣ በቡኢ 3.0 እና በአርሲሮቤ 2.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather was observed in most of the country. Consequently, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Debaarq 4.5, Wegeltena 1.8, Ambamariam 4.0, Mehalmeda 1.0, Alemketema 3.8, Enewari 2.5, Debrebrehan 2.6, Bishoftu 1.2, Bui 3.0 and Arsirobe 2.0.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በአፅቢ፣ በአይደር፣ በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በአዴት፣ በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእንድብር፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will dominate over the north, north east, north west, central and eastern parts of the country. As a result, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Atsebi, Aider, Maichew, Debark, Dangila, Adet, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketama, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Indibir, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jijiga, with continued cold conditions during the night and morning. In contrast, occasional cloud coverage is anticipated over the southwest and southern areas of our country.