Daily Weather Report 24 Dec 14

Weather Summary for previous day

Dec. 13, 2024

በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአይደር 4.2፣ በማይጨው 3.0፣ በወገልጤና 2.6፣ በአምባማሪያም 3.2፣ በኮምቦልቻ 4.6፣ ወራኢሉ 4.8፣ በመሀልመዳ 0.2፣ በአለምከተማ 4.8፣ በእነዋሪ 3.5፣ በደብረብርሀን 0.2፣ በቢሾፍቱ 1.0፣ በቡኢ 2.0፣ በእንድብር 4.6፣ በአርሲሮቤ 3.0 እና በባሌሮቤ 4.8 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions was observed in all parts of the country. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5°C in Aider 4.2, Maichew 3.0, Wegeltena 2.6, Ambamariam 3.2, Combolcha 4.6, Wareilu 4.8, Mehalmeda 0.2, Alemketema 4.8, Enewari 3.5, Debrebrehan 0.2, Bishoftu 1.0, Bui 2.0, Indibir 4.6, Arsirobe 3.0 and Balerobe 4.8.

Weather Forecast for next day

Dec. 15, 2024

በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአዲግራት፣ በአይደር፣ በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በአዴት፣ በወገልጤና፣ በኮምቦልቻ፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእንድብር፣ በአደሌ፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች የሚስተዋልባቸው ሲሆን የማለዳና የሌሊት ቅዝቃዜ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will be observed over most parts of our country. Accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Adigrat, Aider, Maichew, Debark, Adet, Wegeltena, Combolcha, Bati, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Bishoftu, Bui, Indibir, Adele, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jijiga and the morning and night cold will continue the same conditions. Conversely, cloud coverage will be in the southwestern and southern parts of the country.