Daily Weather Report 24 Dec 13

Weather Summary for previous day

Dec. 14, 2024

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከልም በአዲግራት 2.0፣ በማይጨው 4.8፣ በደባርቅ 4.5፣ በወገልጤና 3.8፣ በአምባማሪያም 4.0፣ በባቲ 4.4፣ በደብረብርሀን -0.4፣ በመሀልመዳ 3.2፣ በአለምከተማ 4.8፣ በእነዋሪ 3.5፣ በሾላገበያ 4.0፣ በቢሾፍቱ 3.0፣ በቡኢ 2.0፣ በሐሮማያ 1.2፣ በባሌሮቤ 4.8 እና በጂጂጋ 4.2 ይጠቀሳሉ፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions prevailed in most of the country. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5 °C in the northern, northeastern, central, and southern parts of the country. Among the stations where the daily minimum temperature was recorded below 5 °C Adigrat 2.0, Maichew 4.8, Debark 4.5, Wegeltena 3.8, Ambamariam 4.0, Bati 4.4, Debrebrehan -0.4, Mehalmeda 3.2, Alemketama 4.8, Enewari 3.5, Sholagebeya 4.0, Bishoftu 3.0, Bui 2.0, Haromaya 1.2, Balerobe 4.8, and Jijiga 4.2 are mentioned.

Weather Forecast for next day

Dec. 14, 2024

በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በአፅቢ፣ በአይደር፣ በማይጨው፣ በአዴት፣ በወገልጤና፣ በኮምቦልቻ፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእንድብር፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will be observed over most parts of our country. Accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Atsebi, Aider, Maichew, Adet, Wegeltena, Kombolcha, Bati, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Indibir, Balerobe, Haromaya and Jijiga, with continued cold conditions during the night and morning. In contrast, cloud coverage will be in a few parts of the southwest and south of our country.