Daily Weather Report 24 Dec 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በአብዛኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያይዘ በአድግራት 2.0፣ በማይጨዉ 4.8፣ በደባርቅ 4.5፣ በባቲ 4.4፣ በአምባ ማርያም 4.0፣ በመሀል መዳ 3.2፣ በእንዋሪ 3.5፣ በደብረ ብርሀን -0.4፣ በፍቼ 4.8፣ በሾላ ገበያ 4.0፣ በሐሮማያ 1.2፣ በጅግጅጋ 4.2፣ በቢሾፍቱ 3.0፣ በቡኢ 2.0 እና በባሌ ሮቤ 4.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, most parts of our country experienced by Bega’s dry, sunny and windy weather conditions. In association with this, the lowest daily temperatures were recorded below 50C in Adigrat 2.0, Maichew 4.8, Debark 4.5, Bati 4.4, Amba Mariam 4.0, Mehal Meda 3.2, Anwari 3.5, Debre Berhan -0.4, Fiche 4.8, Shola Gebeya 4.0, Haromaya 1.2, Jigjiga 4.2, Bishoftu 3.0, Bui 2.0 and Bale Robe 4.6.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በሰሜን፣በሰሜን ምስራቅ፣በሰሜን ምዕራብ፣በመካከለኛ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀል መዳ፣ በወራ ኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በኮምቦልቻ፣ በወገል ጤና፣ በማይጨዉ፣ በአድግራት፣ በፍቼ፣ በአሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በአደሌ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቡኢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለዳዉ ቅዝቃዜም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በለላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ በማሻ፣ ቴፒ፣ ሸካ፣ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For tomorrow the Bega’s dry, sunny and windy weather will be observed in the north, northeast, northwest, central and eastern parts of our country. Therefore, in Debre Berhan, Shola Gebeya, Enwari, Mehalmeda, Wereilu, Amba Mariam, Combolcha, Wegel Tena, Maichew, Adigrat, Fiche, Haromaya, Arsi Robe, Adele, Bishoftu, Bale Robe, Bui and Jigjiga, the minimum temperature the day will be below 50C and the night and morning coldness of temperatures will remain cold. On the other hand, there will be cloud coverage in the south and southwest parts of the country. In line with this, there will be light rain in Masha, Tepi, Sheka, Bench Sheko, West Omo, Kefa and Konta zones.