Daily Weather Report 24 Dec 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከልም በዳንግላ 4.5፣ በአዴት 4.2፣ በወገልጤና 2.5፣ በአምባማሪያም 4.0፣ በባቲ 4.2፣ በመሀልሜዳ 3.5፣ በአለምከተማ 4.0፣ በእንዋሪ 3.6፣ በደብረብርሀን 1.8፣ በሾላገበያ 1.0፣ በቢሾፍቱ 3.1፣ በቡኢ 2.4፣ በእንድብር 4.8፣ በሐሮማያ 1.2 እና በጅግጅጋ 1.2 ይጠቀሳሉ፡፡
Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather condition prevailed in all parts of the country Accordingly, the daily minimum temperature dropped below 5 °C over Dangila 4.5, Adet 4.2, Wegeltena 2.5, Ambamariam 4.0, Bati 4.2, Mehalmeda 3.5, Alemketema 4.0, Enewari 3.6, Debrebrihaan 1.8, Sholagebeya 1.0, Bishoftu 3.1, Bui 2.4, Indibir 4.8, Haromaya 1.2 and Jijiga 1.2.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአፅቢ፣ በማይጨው፣ በአዴት፣ በነፋስመዉጫ፣ በባህርዳር፣ በወገልጤና፣ በኮምቦልቻ፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእንድብር፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ማጃንግ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
The next day, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will prevail over most areas of our country. In line with this, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop below 5°C in Atesbi, Maichew, Adet, Nefasmewcha, Bahirdar, Wegeltena, Kombolcha, Bati, Ambamariam, Mehalmeda, Debrebrihaan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Indibir, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jijiga, with continued cold conditions during the night and morning. In contrast, there will be cloud coverage in the southwest and south parts of the country, with light rain expected in the Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, and Majang zones.