Daily Weather Report 24 Dec 10

Weather Summary for previous day

Dec. 9, 2024

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በባህር ዳር 4.6፣ መሃል ሜዳ 3.0፣ ሾላ ገበያ 2.0፣ ቡኢ 2.5፣ ቢሾፍቱ 2.2፣ ደ/ብርሃን -0.2 ፣ ፍቼ 4.0፣ አምባ ማርያም3.5፣ አለም ከተማ 3.2፣ ሐሮማያ 2.0፣ ጅግጅጋ 3.0 እና ባቲ 4.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday dry, sunny and windy Bega weather was observed in most parts of the country. In relation to this, Bahr Dar 4.6, Mehal Meda 3.0, Shola Gebeya 2.0, Bui 2.5, Bishoftu 2.2, D/Berhan -0.2, Fiche 4.0, Amba Maryam 3.5, Alem Ketema 3.2, Haromaya 2.0, Jigjiga 3.0 and Bati 4.0 are the lowest temperatures of the day. The temperature was recorded as below 5oC.

Weather Forecast for next day

Dec. 11, 2024

በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሁሉም የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በባህር ዳር፣ በደባርቅ፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በኮምቦልቻ፣ በአምባማርያም፣ በወረኢሉ፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአደሌ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆንና፤ ከዚሁ ጋር በተየያዘም የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow dry, sunny, and windy Bega weather will be observed in all parts of our country. Thus, in Bahr Dar, Debark, Wegeltena, Bati, Kombolcha, Amba Mariam, Wareilu, Malmeda, Debre Berhan, Enewari, Alem Ketema, Shola Gebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Adele, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya and Jigjiga, the minimum temperature of the day will be below 5oC; At the same time, numerical forecast data indicate that the coldness of the night and the morning will continue in the same condition. On the other hand, there will be cloud cover in a few western and southern areas of our country.