Daily Weather Report 24 Dec 09

Weather Summary for previous day

Dec. 8, 2024

በትናንትናው ዕለት አብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከልም ሾላገበያ 2.0፣ መሀልሜዳ 3.0፣ አለም ከተማ 3.2፣ እንዋሪ 3.5፣አምባ ማርያም 3.5፣ ባቲ 4.0፣ ባህርዳር 4.6፣ ቢሾፍቱ 2.2፣ ቡኢ 2.5፣ ሐሮምያ 2.0፣ ፊቼ 4.0 እና ጅግጅጋ 3.0 እንዲሁም በደ/ብርሀን -0.2 ከዜሮ ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather condition prevailed in most parts of the country. In this regardes, the stations where the daily minimum temperature was recorded as below 5°C were Sholagebeya 2.0, Mehalmeda 3.0, Alemketema 3.2, Enwari 3.5, Amba Mariam 3.5, Bati 4.0, Bahir Dar 4.6, Bischoftu 2.2, Bui 2.5, Haromiya 2.0, Fiche 4.0 and Jijiga 3.0 as well as Debre Birhan -0.2 below zero degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Dec. 10, 2024

በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በኮምቦልቻ፣ በአምባማርያም፣ በወረኢሉ፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በባህር ዳር፣ በደባርቅ፣ በነፋስ መውጫ፣ በፊቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአደሌ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ፣ በጅግጅጋ እና በእምድብር የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን እና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be dry, sunny and windy weather conditions over most parts of our country. In association with this, forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 5oC in Wegeltena, Bati, Combolcha, Ambamariam, Wereilu, Mihalmeda, Debre Beirhan, Enwari, Alemketema, Shola Gebeya, Bahir Dar, Debark, Nefas Mewicha, Fiche, Bischoftu, Bui, Adele, Arsi Robe, Bale Robe, Haramaya, Jijiga and Endibr. On the other hand, there will be occasional cloud cover over the southern parts of the country.