Daily Weather Report 24 Dec 06

Weather Summary for previous day

Dec. 5, 2024

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከልም በደባርቅ 3.5፣ በአምባማሪያም 4.2፣ በደብረብርሀን 0.0፣ በመሀልመዳ 2.8፣ በአለምከተማ፣ 4.2፣ በእነዋሪ 4.5፣ በሾላገበያ 1.0፣ በፍቼ 3.8፣ በቡኢ 3.4፣ በሐሮማያ እና በጂጂጋ 1.4 ይጠቀሳሉ፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather conditions prevailed across most of the country. Accordingly, the daily minimum temperature dropped below 5 °C in the northern, northeastern, central and southern parts of the country. Among the stations where the daily minimum temperature was recorded below 5 °C Debark 3.5, Ambamariam 4.2, Debrebrihaan 0.0, Mehalmeda 2.8, Alemketema 4.2, Enewari 4.5, Sholagebeya 1.0, Fiche 3.8, Bui 3.4, Haromaya and Jijiga 1.4 are mentioned.

Weather Forecast for next day

Dec. 7, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸኮ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ እና ከሶማሌ ክልል የጃራር እና ዶሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage over the western and southeastern parts of the country. In this regard, from the Oromia region Ilubabor; from south west Ethiopia region Bench Sheko and Sheka; from Gambella region Agnuak and Majang and Somali region Jarar and Dollo zones will receive light rain at a few places. On the other hand, the Bega dry, sunny and windy weather conditions prevail in our country's northeastern, eastern and central parts. In line with this, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud dropped below 5 °C.