Daily Weather Report 24 Dec 05

Weather Summary for previous day

Dec. 4, 2024

በትናንትናው ዕለት በጋምቤላ የደመና ሽፋን የነበረ ሲሆን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ 4.5፣ ወገልጤና 3.0፣ መሃል ሜዳ 2.5፣ ደ/ብርሃን 0.2፣ ሾላ ገበያ 2.0፣ ቢሾፍቱ 5.0፣ ሐሮማያ 2.0፣ ቡኢ 3.0 እና ጅግጅጋ 4.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was cloud cover in Gambella and light rainfall was recorded. On the other hand, dry, sunny and windy summer weather has been observed in the northeast, east and central regions of our country. In relation to this, in Debark 4.5, Wegeltena 3.0, Mehal Meda 2.5, De/Berhan 0.2, Shola Gebeya 2.0, Bishoftu 5.0, Haromaya 2.0, Bui 3.0 and Jigjiga 4.6, the lowest temperature of the day was recorded as below 5oC.

Weather Forecast for next day

Dec. 6, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ይጠበቃል፡፡

Tomorrow there will be cloud cover over the western parts of the country. Therefore, Ilubabor from Oromia region; Sheka, Bench Sheko and West Omo regions of Southwest Ethiopia and the Majang and Anuwak zones of Gambella region will receive light rainfall. On the other hand, the north-east, east and central areas of our country will have dry, sunny and windy Bega weather, and in this regard, the minimum temperature of the day is expected to be below 5oC.