Daily Weather Report 24 Dec 04

Weather Summary for previous day

Dec. 3, 2024

በትናንትናው ዕለት ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በደባርቅ፣ ቻግኒ እና ጋምቤላ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አምባ ማርያም፣ መሃል ሜዳ፣ አለም ከተማ፣ ደ/ብርሃን፣ ሾላ ገበያ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ እና ጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, North Gondar, West Gojam and Gambella had cloud cover and light rain was recorded in Debark, Chagni and Gambella. On the other hand, dry, sunny and windy Bega weather has been observed in the northeast, east and central areas of our country. In relation to this, Amba Maryam, Mehal Meda, Alem City,

De/ Berhan, Shola Market, Bishoftu, Bui and Jigjiga recorded the lowest temperature of the day below 5oC.

Weather Forecast for next day

Dec. 5, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። ስለሆነም ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover over the western parts of the country. Therefore, Ilubabor from Oromia region; The Sheka, Bench Sheko and West Omo regions of Southwest Ethiopia and the Majang and Anuwak zones of Gambella region will receive light rainfall. On the other hand, the northeast, east and central regions of our country will have dry, sunny and windy Bega. In this regard, forecast indicates that the minimum temperature of the day will be below 5oC.